የሀገር ውስጥ ዜና

ኮርፖሬሽኑ ለንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ማዘጋጃ የሚውል በቂ ቴክኒካል አልኮል መኖሩን አስታወቀ

By Tibebu Kebede

March 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኳር ኮርፖሬሽን ለንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ማዘጋጃ የሚያገለግል ከ3 ሚሊየን ሊትር ቴክኒካል አልኮል መኖሩን አስታወቀ።

ኮርፖሬሽኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አልኮሉ በፊንጫ እና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች እንደሚገኝ አስታውቋል።

አሁን ላይም ፋብሪካዎቹ በቀን 100 ሺህ ሊትር ቴክኒካል አልኮል በማምረት ላይ መሆናቸውን ጠቅሶ፥ አልኮሉ የዓለም ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ የንጽህና መጠበቂያዎችን ለማምረት እንደሚውል ገልጿል።

በቂ የቴክኒካል አልኮል ክምችት መኖሩን የጠቀሰው ኮርፖሬሽኑ ከጤና እና ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር ከዚህ ቀደም ይወስዱ ከነበሩ ድርጅቶች በተጨማሪ ሰባት ድርጅቶች አልኮል እንዲወስዱ ተፈቅዷልም ነው ያለው።

ቴክኒካል አልኮል ለሳኒታይዘር፣ ለደረቅና ፈሳሽ ሳሙና እንዲሁም ለመጸዳጃ ቤት ማጽጃ መስሪያ በግብዓትነት ያገለግላል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision