የሀገር ውስጥ ዜና

“ኑ የጋራ ቤታችንን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የወጣቶች የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

September 22, 2022

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል እና ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በጋራ ያዘጋጁት “ኑ የጋራ ቤታችንን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የወጣቶች የፓናል ውይይት በካፒታል ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በፓናል ውይይቱ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ ጋዜጠኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ መሆናቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።