አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጸደይ ባንክ በመጪው ቅዳሜ በ11 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ካፒታል ሥራ እንደሚጀምር የባንኩ ቦርድ ገልጿል።
ባንኩ ሥራ ለመጀመር የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ ማጠናቀቅ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።
የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር ገዱ አንዳርጋቸው ÷ ጸደይ ባንክ 11 ቢሊየን ብር ግዙፍ ካፒታል ይዞ በመጪው ቅዳሜ በ148 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሥራ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን የለውምወሰን በበኩላቸው ÷ባንኩ የተሳለጠ አገልግሎት መሥጠት ይችል ዘንድ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ የታጠቀ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ባንኩ 7 ነጥብ 8 ቢሊየን የተከፈለ ጠቅላላ ካፒታል ይዞ ሥራ ይጀምራል ነው ያሉት።
ጸደይ ባንክ በአጠቃላይ 46 ቢሊየን የሚገመት ሃብት ያለውና በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም ገልጸዋል።
ባንኩ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ባንክ እንደመሆኑ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ቅርጫፎችን ይከፍታል መባሉንም አሚኮ ዘግቧል፡፡