አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በዞኑ አልከሶ 01 ቀበሌ መኒታ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 6 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና በ3 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ ገልጿል፡፡
የወራቤ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ አስተባባሪ ምክትል ሳጅን ቢላል አወል እንደገለጹት÷ አደጋው የተከሰተው ሀይሉክስ ተሽከርካሪ ከባለሶስት እግር ተሽከርካሪ በመጋጨቱ ነው ብለዋል።
ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ህፃን ልጅ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን÷ በወራቤ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡
የአደጋው መንስኤም በመጣራት ላይ መሆኑን ምክትል ሳጅን ቢላል አወል መናገራቸውን ከወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።