የሀገር ውስጥ ዜና

የጋሞ ብሔር የዘመን መለወጫ “ዮ ማስቃላ” በድምቀት እየተከበረ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

September 25, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2015 ዓ.ም የጋሞ ብሔር የዘመን መለወጫ “ዮ ማስቃላ” በአርባምንጭ ከተማ በድምቀት ሁኔታ በመከበር ላይ ነው፡፡

በበዓሉ ላይ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዎች የሆኑት ብርቱካን አያኖ እና አምባሳደር ተስፋዬ ይልማን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዞኑ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡