ስፓርት

አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸነፈች

By ዮሐንስ ደርበው

September 25, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በበርሊን በተካሄደው 48ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፋለች፡፡

አትሌት ትዕግስት 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ነው የቦታው አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበችው፡፡