የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለ15 ቀን የታራሚዎችን ቤተሰብ ጥየቃ ማገዱን አስታወቀ

By Tibebu Kebede

March 19, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ታራሚዎችን ለመጠበቅ ሲባል ለመጭዎቹ 15 ቀናት ታራሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ እግድ መጣሉን አስታውቋል።

የማረሚያ ቤቱ ጄኔራል ኮሚሽነር ጀማል አብሶ እንደገለጹት፥ ክልከላው ለመጭዎቹ 15 ቀናት ተግባራዊ ይደረጋል።