የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ከነገ እስከ እሁድ ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር አይቻልም

By ዮሐንስ ደርበው

September 29, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ምክንያት ከነገ አርብ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደማይቻል ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመት ኤጀንሲ እንዳስታወቀው÷ ቅደሜ መስከረም 21 ቀን 2015 ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል በሁሉም የመዲናዋ በሮች የሚገቡ የበዓሉ ታዳሚዎች ስለሚኖሩ ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የሞተር ብስክሌት እንቅስቃሴን መገደብ አስፈልጓል።