የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለካናዳ ገዢ አቀረቡ

By Melaku Gedif

September 30, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለካናዳዋ ገዢ ሜሪ ሳይመን አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር ፍጹም በኢትዮጵያ እና ካናዳ መካለል ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም አምባሳደሩ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ለካናዳዋ ገዢ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡