የሀገር ውስጥ ዜና

የሲዳማ ክልል ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት የ26 ሚሊየን ብር የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረገ

By Alemayehu Geremew

September 30, 2022

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የ26 ሚሊየን ብር የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ÷ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ አንድነት ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እየታገለ ለሚገኘው ጀግናው ሰራዊታችን ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ ክብር አለን ብለዋል።

የሲዳማ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ኤልያስ ÷ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደጀንነታችንን ለማሳየት 20 ሚሊየን የገንዘብና 6 ሚሊየን የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አድርገናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።