አዲስ አበባ ፣ መስከረም 23 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከምባታ ጠምባሮ እና የሀላባ ዞኖች ለመከላከያ ሰራዊት የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡
አሸባሪው ህወሓት የከፈተውን ጦርነት ለመቀልበስ በግንባር እየተዋጋ ለሚገኘው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከ6 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት እና 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ደግሞ በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
የከምባታጠምባሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መለሰ አጭሶ÷በብርቱ ክንዱ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን እየደቆሰ ላለው ለመከላከያ ሠራዊት ከዞኑ ሕዝብ የሚደረገው ድጋፍ እስከ ጦርነቱ ፍፃሜ ድረስ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ የሀላባ ዞን በ2ኛ ዙር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የተለያየ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ ከ40 በላይ ሰንጋዎች፣ 40 በላይ በግ እና 80 ኩንታል በሶና ዱቄት ሌሎች ድጋፎችን ያካተተ መሆኑን ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!