የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

By Tibebu Kebede

March 20, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር እስክንድር ሳህሉ እስካሁን የቫይረሱ ምልክት ታይቶባቸው ወደ ሆስፒታሉ የመጡ ታማሚዎች አለመኖራቸውን ተናግረዋል።

ይሁን እንጅ የቫይረሱ ምልክት የታየባቸው ሰዎች ወደ ሆስፒታሉ ቢመጡ ወደ ማቆያ ክፍል እስከሚሄዱ ድረስ ተገልለው የሚቆዩበት ቦታ መዘጋጀቱንም ነው የተናገሩት።

አያይዘውም የሳምባ ምች (ኒሞኒያ)፣ የመተንፈሻ አካል ችግር፣ ሳል፣ ትኩሳት እና የጉዞ ታሪክ ያላቸውን በጥርጣሬ እንዲያዩ እና ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሏቸው ለህክምና ባለሙያዎች ትዕዛዝ መሰጠቱንም ገልጸዋል።

የቫይረሱ ምልክቶች ያለባቸው ባጋጠሙ ጊዜ በሆስፒታሉ የመጀመሪያ እርዳታ ከተሰጠ በኋላ ለበለጠ ምርመራ ወደ ተዘጀጋጁላቸው ማዕከላት እንዲላኩ ይደረጋልም ነው ያሉት።

መረጃው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ነው

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision