አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ፌዴሬሽን ምክር ቤት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም 6ኛ የፓርላማ ዘመን 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡
የምክር ቤቱ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ተረፈ በዳዳ እንደገለጹት÷ ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባዔው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡