የሀገር ውስጥ ዜና

ዩኒቨርስቲዎች የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን መቀበላቸውን ቀጥለዋል

By Mikias Ayele

October 08, 2022

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው፡፡

 

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘጠኝ ካማፓሶች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

 

በተመሳሳይ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ÷ የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው ፡፡

 

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲም÷ 37ሺህ ተፈታኝ ተማሪዎች የሚቀበል ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት ቅበላ እንደተደረገላቸው ታውቋል።

 

ደብረ ማርቆስ፣ አሶሳ እና ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲዎችም ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ተፈተኛ ተማሪዎችን እየተቀበሉ እንደሚገኙ መግለጻቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡