አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በካናዳና አሜሪካ በሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አደረጃጀቶች በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ባዘጋጁት የድጋፍ ማሰባሰቢያ የበይነ-መረብ መርሐ-ግብር ከ110 ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰባቸው ተገለጸ፡፡
ድጋፉ የተሰበሰበው ‘ድር ቢያብር አንበሳ ያስር’ በሚል መርህ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡
በካናዳ የኢፌዴሪ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ÷ ድጋፉ እንዲሰባሰብ ላስተባበሩ የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ኢክናስ ካናዳ፣ ፒቱፒ እና ለሌሎች አጋር አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ለተጎጂ ወገኖች ድጋፍ ለማሰባሰብ የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።