የሀገር ውስጥ ዜና

ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በመዲናዋ የምርት እጥረት ቢከሰት ከአርሶ አደሮች ምርቶችን በመረከብ ለተጠቃሚው በቀጥታ ይቀርባል- ከተማ አስተዳደሩ

By Tibebu Kebede

March 21, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስን (በማስመልከት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ፣ ንግድ ቢሮ እና የትራንስፖርት ቢሮ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ከንግድ ጋር በተያያዘ መግለጫ የሰጡት የንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ መሀመድ በከተማዋ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እና የአቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር የከተማ አስተዳደሩ ግብረ ሃይል አቋቁሞ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል ብለዋል።