የሀገር ውስጥ ዜና

ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ መንገደኞች የ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ ሰኞ መተግበር ይጀምራል

By Tibebu Kebede

March 21, 2020

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡ ሁሉም መንገደኞች ላይ ተፈፃሚ የሚሆነው የ14 ቀናት በልዩ ማቆያ የመቆየት ግዴታ የፊታችን ሰኞ መተግበር እንደሚጀምር የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እነዚህ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች በስካይ ላይት እና ጊዮን ሆቴሎች ለ14 ቀናት ተለይተው ይቆያሉ።