የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል ለሥራ ዕድል ፈጠራ ለሚያደርገው ጥረት ድጋፋችን ይቀጥላል- ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

By ዮሐንስ ደርበው

October 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ለሥራ ዕድል ፈጠራ እያደረገ ያለው ጥረት ውጤታማ በመሆኑ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሚደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ካቢኔ በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ተወያይተዋል፡፡