የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ የሣይንስ ሙዚየምን ጎበኙ

By Tamrat Bishaw

October 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያ የሚገኙት የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ በቅርቡ የተመረቀውን የሣይንስ ሙዚየም ጎበኙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ የፓንአፍሪካን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ 2022 ዐውደ ርዕይን እና በሣይንስ ሙዚየም ለዕይታ የቀረቡ የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጎብኘታቸውን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ በጉብኝቱ ወቅት ኤግዚቢሽኑ የአፍሪካን ወንድማማችነት የሚወክል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መሰል መድረኮች አፍሪካን በሣይንስና በቴክኖሎጂ የላቀች አህጉር ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳቸውም ጠቁመዋል፡፡