የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር ይናገር ደሴ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Amele Demsew

October 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ሌሎች የአፍሪካ ማዕከላዊ ባንክ ገዥዎች በተገኙበት ከዓለም የገንዘብ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂዩቫ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ በአፍሪካ ወቅታዊ የኢኮኖሚ ችግሮች፣ በተለይም የዕዳ ጫና መቀነስ ስለሚቻልበት፣ የነዳጅ እና የመሠረታዊ ምርቶች ዋጋ መናርን ለመቋቋም መወሰድ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ በሚገኘው ዓመታዊ የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እየተመራ በተለያዩ መድረኮች እየታሳተፈ እንደሚገኝ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲመረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!