የሀገር ውስጥ ዜና

የጣና ፎረም ጉባኤ ተሳታፊዎች በጣና ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

By Amele Demsew

October 16, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ ተሳታፊዎች በጣና ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል፡፡

10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ ከትናንት ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ከጉባኤው ጎን ለጎን ተሳታፊዎች በዛሬው ዕለት በጣና ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ማከናወናቸውን ከጣና ፎረም አዘጋጆች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡