የሀገር ውስጥ ዜና

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጎንደር ከተማ እየተገነባ ያለውን የዳቦ ፋብሪካ ጎበኙ

By Feven Bishaw

October 16, 2022

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጽህፈት ቤታቸው አማካኝነት በጎንደር ከተማ እየተገነባ ያለውን የዳቦ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት ጎበኙ።

ፋብሪካው በዋናነት በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

የፋብሪካው ግንባታ ከተጀመረ 7 ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን÷ በጥር ወር 2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገባ በቀን እስከ 200 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም እንደሚኖረው መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡