የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አከበሩ

By Meseret Awoke

October 17, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሠራዊት አባላት 15ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበሩ።

ቀኑ ጦር ሃይሎች በሚገኘው የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ግቢ የተከበረ ሲሆን ፥ የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂም ፣ ከፍተኛ መኮንኖችና የሠራዊቱ አባላት ተገኝተዋል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጄነራል ይመር መኮንን በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፥ ጥንት አባቶች በትውልድ ቅበብሎሽ በከፈሉት መስዋዕትነት ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ አድርገው አቆይተዋል።

የአሁኑ ትውልድም የሀገር ዳር ድንበርን በማስከበር ረገድ አኩሪ ስራ ማከናወኑንም ነው የተናገሩት።

በቀጣይም አስፈላጊውን ሁሉ መስዋዕትነት ለመክፈል ሠራዊቱ ዝግጁ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!