የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ከህንድ አቻቸው ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

October 17, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ከህንድ መከላከያ ሚኒስትር ራጅኔት ሲንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ በህንድ እየተካሄደ በሚገኘው የህንድ-አፍሪካ የመከላከያ ምክክር መድረክ ጎን ለጎን ነው የተወያዩት፡፡

በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል የተመጀሩ የወታደራዊ አቅም ግንባታ ስራዎችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ህንድ እና ኢትዮጵያ በመከላከያው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው ለመቀጠል ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡