የሀገር ውስጥ ዜና

ፈረንሳይ የቅዱስ ላሊበላ አብያተክርስቲያትን ለማደስ የ5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

By ዮሐንስ ደርበው

October 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ መንግሥት የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን ለማደስና ለመጠበቅ አገልግሎት የሚውል የ5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ፡፡

የዛሬው የድጋፍ ስምምነት÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከአራት ዓመት በፊት በሀገሪቱ ያለውን ቅርስ ለመጠበቅ ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ የተደረገ ነው፡፡