አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ- ጂቡቲ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ሁለተኛ ሰርኪዩት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ÷ ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ለጂቡቲ ደግሞ በተመጣጣኝ ዋጋ ኤሌክትሪክ በማግኘት የሀገሪቱን ኢንዱስትሪ ለማነቃቃት እና የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋት ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡