የሀገር ውስጥ ዜና

ነገ በመዲናዋ ለሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ

By Shambel Mihret

October 21, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ።

“ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ድምፄን አሰማለሁ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ከተሞች ጥቅምት 12 እና 13 ቀን 2015 ዓ.ም የድጋፍ ሰልፍ እንደሚካሄድ ይታወቃል።

ህዝባዊ ሰልፉ መንግስት የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት ለማስከበር የሚያደርገውን የመከላከል እርምጃ የሚደግፍ እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ነው ተብሏል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት 12 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ የጋራ ግብረ ሃይሉ አስታውቋል።

የድጋፍ ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

በዚህ መሠረትም ፡-

ስለሆነም አሽከርካሪዎች ይህንኑ አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ እንዲሁም ከአርብ ምሽት ጀምሮ ተሽከርካሪ ማሳደር ፍፁም ክልክል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ  መረጃ ያመላክታል፡፡

ህብረተሰቡም የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 0111 -11- 01 -11፣ 0111- 26- 43- 59 እንዲሁም በ0111- 01- 02- 97፣ መጠቀም እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡