የሀገር ውስጥ ዜና

የጅቡቲ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

By Meseret Awoke

October 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጅቡቲ የሚኒስትሮች ኮሚሽን የጋራ ስብሰባ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገባ፡፡

ቡድኑ አዲስ አበባ የገባው በኢትዮ- ጅቡቲ ጥምር የሚኒስትሮች የኮሚሽን ስብሰባ ላይ ለመካፈል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ለልዑካን ቡድኑ የኢፌዴሪ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!