የሀገር ውስጥ ዜና

የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር የሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ

By Melaku Gedif

October 28, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ16ኛው የኢትዮ-ጂቡቲ የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ የተሳተፉት የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሃመድ አሊ ዩሱፍ ሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ።

በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ መካከል ያለው ጠንካራ እና ታሪካዊ ግንኙነት በቴክኖሎጂና በሳይበር ደህንነት መስክም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሚኒስትሩ መሃመድ አሊ ዩሱፍ በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በሳይንስ ሙዚየም ለእይታ የቀረቡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የሌሎች ተቋማትን ምርትና አገልግሎቶችን መመልከታቸውንም ከኢመደአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!