የሀገር ውስጥ ዜና

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ተወሰነ

By Tibebu Kebede

March 24, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መወሰኑን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሳይንስ እና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ተወስኗል።