የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት 2ኛ ዓመት ታሰበ

By Feven Bishaw

November 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ “መቼም አንረሳውም” በሚል መሪ ቃል በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ ተካሄደ፡፡

ዕለቱ በደም ልገሳ፣ ጧፍ በማብራት እና ቀኝ እጅን ግራ ደረት ላይ በማድረግ መታሰቡን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ ባደረጉት ንግግር÷ በዚህ ቀን በዋጋ የማይተመን ሕይወታቸውን ስለሀገር ክብር መስዋዕትነት የከፈሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን አንረሳም ብለዋል፡፡