የሀገር ውስጥ ዜና

የጅቡቲው ፕሬዚዳንት በመንግስት እና በህወሓት የተደረሰውን የሰላም ሰምምነት አደነቁ

By Amele Demsew

November 03, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በአፍሪካ ህብረት አሸማጋይነት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አድንቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ለቀጠናው ሰላም እና ለኢትዮጵያውያን ወንድም ህዝቦች ደህንነት፣ ሰላምና ብልጽግና ሲባል ለተደረገው የሰላም ስምምነት ጥረት ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡