ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ወላይታ ድቻ እና ወልቂጤ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

By Alemayehu Geremew

November 05, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ድሬዳዋ ላይ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

10 ሰዓት ላይ ወላይታ ድቻ እና መቻል ባደረጉት ጨዋታ ወላይታ ድቻ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ግብ ቃልኪዳን ዘላለም በ31ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ወልቂጤ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የወልቂጤ ከተማን ማሸነፊያ ግቦች ጌታነህ ከበደ በ21ኛው እና 52 ኛው ደቂቃ ላይ ሲያሥቆጥር÷ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ደግሞ ታፈሰ ሰርካ በተጨማሪ ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡