የሀገር ውስጥ ዜና

የአርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአርቲስቱ ቤት ሽኝት ተደረገለት

By ዮሐንስ ደርበው

November 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የክብር ዶ/ር አርቲስት ዓሊ ቢራ አስክሬን ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአርቲስቱ ቤት ሽኝት ተደረገለት፡፡

ዛሬ ለአንጋፋው አርቲስት ዓሊ ቢራ የጀግና የክብር ሽኝት ከተደረገለት በኋላ ሥርዓተ ቀብር ይፈጸማል፡፡

አስከሬኑ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ እስጢፋኖስ፤ ከዚያም በሠረገላ ወደ ወዳጅነት አደባባይ አምርቷል።

በወዳጅነት አደባባይ የጀግና ስንብት ከተደረገለት በኋላም ወደ ድሬዳዋ አስክሬኑ ተሸኝቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!