የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የፖላንድ ኤምባሲ ለአብርሆት ቤተ-መፃሕፍት የተለያዩ መፃሕፍትን አበረከተ

By Feven Bishaw

November 09, 2022

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፖላንድ አምባሳደር ፕርዜምስታው ቦባክን ጨምሮ ሌሎች የኤምባሲው ተወካዮች በተገኙበት መፃሕፍቶችን ለአብርሆት ቤተ-መፃሕፍት ኃላፊ ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ አበርክተዋል።

አምባሳደሩ ዛሬ ከተደረገው የመጻህፍት እገዛ ባለፈ በቀጣይ ተቋሙን በተለያዩ ዘርፎች ለመርዳትና ለማገዝ ቃል ገብተዋል፡፡

የቤተ-መፃሕፍቱ ሃላፊ ኢንጂነር ውባየሁ በበኩላቸው ÷ለሁሉም ጉዳዮች ቁልፍ መሳሪያ ለሆነው ትምህርት ትኩረት በመስጠት አንባቢ ትውልድ መገንባት ወሳኝ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በቀጣይም በጋራ የሚሰሩበትን መድረኮች እንደሚያመቻቹ የገለጹት ሃላፊው ለተደረገው የመጻሕፍት ልገሳም አመስግነዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!