አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2015 የሠላም ስምምነቱ ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ድል እንድትጎናጸፍ ማድረጉን የህግና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ገለጹ።
የውስጥ አለመስማማቶች የውጭ ተጋላጭነትን እንደሚጨምሩ ያነሱት ምሁራኑ የተደረሰው ስምምነት የተጠቀሰውን ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ነው የተናገሩት።
የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት አቶ ንጋቱ አበበ በበኩላቸው ÷ ኢትዮጵያ የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካውያን ለመፍታት ያሳየችው አቋምና በአፍሪካ ጥላ ሥር መፍታቷ አኅጉራዊና ቀጣናዊ ተቀባይነቷን እንደሚጨምረው ጠቅሰዋል።
የኅግ ባለሙያ የሆኑት አቶ አንዷለም በዕውቀቱም ስምምነቱ ከዲፕሎማሲ አንፃር የውጭ ግንኙነት አግባብን ያስተካክላል ብለዋል፡፡
ስምምነቱን ተከትሎ በኅገ መንግስቱ ላይ በሰፈረው መሰረት የውጭ ግንኙነት በፌደራል መንግስቱ ብቻ እንዲከናወን መደረጉ ጣልቃ ገብነትን የሚያስቆም እንደሆነም አብራርተዋል።
እንደ ፖለቲካና ህግ ምሁራኑ ገለፃ ÷ ስምምነቱ የባዕዳንን ጣልቃ የመግባት ሴራ አሸንፎ የሚያሻግር ነው።
የሰላም ስምምነቱን ቱሩፋቶች ለመጠቀም ለተግባራዊነቱ መሥራት እንደሚገባም አስምረውበታል።
በአፈወርቅ እያዩ