የሀገር ውስጥ ዜና

አመራሩ ሕዝብ እና መንግሥት የጣለበትን ኃላፊነት በቁርጠኝነት ሊወጣ ይገባል – አቶ ኦርዲን በድሪ

By Melaku Gedif

November 11, 2022

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ በ2015 የመጀመሪያው ሩብ አመት የተሰሩ ስራዎችን ገምግሟል።

በግምገማው የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት በክልሉ በመጀመሪያው ሩብ አመት አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል።

በተለያዩ ዘርፎች ውስንነት የታየባቸው እና ሊሻሻሉ የሚገባቸው አፈፃፀሞች መኖራቸውን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የአመራሩ ቁርጠኝነት ማነስ ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም የህዝብን ተጠቃሚነት ለማጎልበት በሚከናወኑ ተግባራት አመራሩ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩም የተለያዩ ሀሳቦችና አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን ለመቅረፍ፣ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ለማጎልበት እንዲሁም ተጠያቂነትን ለማስፈን በሚቻልባቸው ጉዳዮች  መግባባት ላይ መደረሱን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡