አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ብርሃን ከተማ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ማስፋፊያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
ማስፋፊያው በ75 ሚሊየን ብር ወጪ የሚገነባ መሆኑ ተገልጿል።
የከተማዋ የመጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ መሰረት መንገሻ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ማስፋፊያው ከ100 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንፁሕ መጠጥ ውኃ ችግር የሚቀርፍ ነው።
የማስፋፊያ ሥራው በአንድ ዓመት እንዲጠናቀቅ መታቀዱን እና ወጪውም በጽሕፈት ቤቱ መሸፈኑን ተናግረዋል፡፡
በዓይናለም ስለሺ