የሀገር ውስጥ ዜና

የስታትስቲክስ መረጃ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ዕድገትና ሥራዎችን ለማሳለጥ ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

November 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስታትስቲክስ መረጃ በአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ሥራዎችን ለማሳለጥ ወሳኝ ድርሻ አለው ሲሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ ገለጹ።

የአፍሪካ ስታትስቲክስ ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው፡፡

ዶክተር ፍጹም አሰፋ በመርሐ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ የስታትስቲክስ መረጃ በአፍሪካ የኢኮኖሚ ሥራዎችን ለማሳለጥ ወሳኝ ድርሻ አለው ብለዋል፡፡

በተለይም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያለው ሚና ወሳኝ በመሆኑ÷ የስታትስቲክስ መረጃ መዘመን ላይ በትኩረት ሊሠራበት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ግብርና ትልቁ የኢኮኖሚ ምንጭና የስራ ዕድል የሚፈጠርበት መሆኑን አንስተው የተጠናከረ የስታትስቲክስ መረጃ ማቅረብ ለስራው መቃናት አጋዥ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም መረጃን በጥራት መሰብሰብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!