የሀገር ውስጥ ዜና

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 252 ተማሪዎችን አስመረቀ

By Melaku Gedif

November 19, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያስተማራቸውን 252 ተማሪዎች አስመረቀ።

ከተመራቂዎቹ መካከል 176ቱ ወንድ ሲሆኑ 76 ደግሞ ሴዮች ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥ 57 ስፔሻሊስት ሀኪሞች መሆናቸውን የኮሌጁ መረጃ ያመላክታል።

በተመሳሳይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሕክምናን ጨምሮ በተለያዩ የጤና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 229 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የሕክምና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ናፍቆት ብርሃኑ ለተመራቂዎች ንግግር አድርገዋል።

አቶ ናፍቆት በንግግራቸው የጤና ሙያን ልዩ የሚያደርገው ከክቡር የሰው ልጅ ህይወት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ መሆኑ ነው ብለዋል።