አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የበለጸጉ ሀገራት በሚለቁት ካርበን ምክንያት የሚደርሰው ብክለት ጉዳት ለሚያደርስባቸው ታዳጊ ሀገራት ማካካሻ ልዩ ፈንድ እንዲቋቋም የመንግሥታቱ የአየር ንብረት ጉባዔ ወሰነ፡፡
ከበለፀጉ ሀገራት በሚለቀቀው በካይ ጋዝ ምክንያት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ለሚደረስባቸው ጉዳት ማካካሻ የሚሆን የ “ኪሳራ እና ጉዳት” ፈንድ በዛሬው ዕለት ፀድቋል።
በግብጽ ሻርም ኤል-ሼክ ሲካሄድ የቆየው የአየር ንብረት ጉባዔ (COP-27) ልዩ የማካካሻ ፈንዱ እንዲቋቋም በማጽደቅ መጠናቀቁን ቲ አር ቲ ወርልድ ዘግቧል፡፡
ልዩ ፈንዱ÷ በበለጸጉ ሀገራት የጋዝ ልቀት ምክንያት የሚደርሰው የሙቀት መጨመር በታዳጊ ሀገራት ላይ ለሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ ማካካሻ የሚሆን ነው፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔ በዓለም ሙቀት መጨመር ምክንያት ለአደጋ በተጋለጡ ሀገራት ላይ የሚደርሰውን ኪሳራ ለመሸፈን ነው ልዩ ፈንዱን ያፀደቀው።
የተለያዩ ሀገራት የአየር ንብረት ጉዳይ ሚኒስትሮችም “ረጅም ዓመታት የወሰደው ጉዞ በመጨረሻም ፍሬ አፍርቷል” በሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ሀገራቱ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ችግር ለመቋቋም እና ለመላመድ የሚያስችሉ ሌሎች የገቧቸው ቃሎች ተፈፃሚ እንዲሆኑ የጉባዔው ሠነድ ጠይቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!