አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን በክልሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተቋቋመው ግብረ ሃይል ገለጸ፡፡
ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው 24 ሰዎች ተለይተዋልም ነው የተባለው።
ግብረ ሃይሉ በህብረተሰቡና በተቋማት የሚታየው ቸልተኝነት አሁንም አሳሳቢ ነው ብሏል።
በትዕግስት አብርሃም
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision