የሀገር ውስጥ ዜና

በምእራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

By Feven Bishaw

March 27, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምእራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ትናንት የደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አስከተለ።

የቤሮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ቦልሳ ከበደ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በአደጋው የሰው ህይወት ባይጠፋም በወረዳው የጋቢሳ ቀበሌ ከ700 በላይ የሚሆኑ አነስተኛ ቤቶች ወድመዋል።

በዚሁ አደጋ ሰዎች  የተፈናቀሉ ሲሆን፥ ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እና የጉዳት መጠን እያጠና ይገኛል።

በታደሰ ሽፈራው