የሀገር ውስጥ ዜና

አብርሆት ቤተ መጻሕፍት እስከ ሌሊት 6 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

By Amele Demsew

November 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አብርሆት ቤተ መጻሕፍት ከነገ ሕዳር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሌሊት 6 ሰዓት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለጸ። የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት ዳይሬክተር ኢንጂነር ውባየሁ ማሞ እንዳሉት÷ ቤተ መጻሕፍቱ አንባቢ ትውልድን ለማፍራት ትልቅ ድርሻ ያለው ፣ ታሪክ ሠሪ ትውልድ በንባብ የሚገነባበት ማዕከል ነው። በንግግርና ውይይት የሚያምን ትውልድ የሚገነባው አንባቢ ትውልድ ሲፈጠር መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡ ቤተ መጻሕፍቱ ከዚህ ቀደም ከጧቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሠዓት ብቻ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር አውስተው ተጠቃሚዎች የአገልግሎት ሰዓት እንዲራዘም በጠየቁት መሰረት እስከ ሌሊት 6 ሠዓት ሊራዘም መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ከጧቱ 2 ሠዓት እስከ ሌሊቱ 6 ሠዓት ድረስ ቤተ መጻሕፍቱ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!