የሀገር ውስጥ ዜና

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ለኮቪድ-19 ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴና ለጤና ሚኒስቴር የተለያዩ ቁሳቁሶች አበረከተ

By Feven Bishaw

March 27, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ለኮቪድ-19 ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ እና ለጤና ሚኒስቴር የቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ፅህፈት ቤቱ 100 ብርድ ልብስ፣ 100 አንሶላ፣ 100 ፍራሽ፣ አምስት ዊልቸር እና ሶስት የጽኑ ህሙማን ለማከም የሚሆኑ ማሽኖች ነው ያበረከተው።

በተጨማሪም ፅህፈት ቤቱ የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ የብሄራዊ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚልና የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ድጋፎቹን ተረክበዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸውም በአካል ድጋፉን አስረክበዋል።

በፍሬህይወት ሰፊው