የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠናና የተልዕኮ አቅጣጫ ሰጡ

By Feven Bishaw

November 23, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠናና የተልዕኮ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ስልዕጠናው በአፍሪካ የአመራር የልህቀት ማዕከል የተሰጠ ነው።

በስልጠናው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተውጣጡ ወጣትና አንጋፋ ዲፕሎማቶች እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች መገኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።