የሀገር ውስጥ ዜና

ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ ተጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

November 24, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአፋር ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች የነበሩ ወገኖችን ወደ መኖሪያ ቀያቸው የመመለስ ሥራ ተጀመረ፡፡

ዛሬ በተጀመረው የመጀመሪያ ዙር ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ በአፋር ክልል÷ ሠመራ፣ ሎጊያ እና ዱብቲ የመጠለያ ጣቢያዎች የነበሩ 738 የትግራይ ተወላጆች ወደ ቀያቸው ተመልሰዋል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ከዞን ሁለት ኪልበቲ ረሱ፣ ባራሕሌ፣ ኮነባ እና ዳሎል የተፈናቀሉ ወገኖችንም ወደ ቀያቸው ለመመለስ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽንቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!