የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 124 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

November 25, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 1 ሺህ 124 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ዜጎቹ ዛሬ በተደረጉ በረራዎች መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ከትናንት በስቲያ 1 ሺህ 21 ዜጎች ከሳዑዲ መመለሳቸው ይታወሳል።

በሁለተኛው ዙር እየተከናወነ ባለው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ የዛሬውን ጨምሮ 3 ሺህ 317 ዜጎችን መመለስ ተችሏል።