ስፓርት

ፈረንሳይ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች

By Amele Demsew

November 26, 2022

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የኳታር የዓለም ዋንጫ ምሽት ላይ ፈረንሳይ እና ዴንማርክ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

በዚህም ፈረንሳይ ዴንማርክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነጥቧን ወደ ስድስት ከፍ አድርጋለች፡፡

የፈረንሳይን የማሸነፊያ ጎሎች ክሊያን ምባፔ በ61ኛው እና 86ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል፡፡

ዴንማርክን ከሽንፈትያላዳነችውን ብቸኛ ጎል ደግሞ አንድሪያስ ክርስቴንሰን በ68ኛውደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡