የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ምክር ቤት ሁለት የካቢኔ አባላት ሹመት አጸደቀ

By Feven Bishaw

November 29, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት ሁለት የካቢኔ አባላትን ሹመት አጸደቀ።

ምክር ቤቱ የትምህርት ደረጃቸውን እና የአመራር ብቃታቸውን መሰረት በማድረግ ለሁለት የካቢኔ አባላት በከፍተኛ ድምጽ ሹመት ሰጥቷል።

በዚህም ዶክተር ኢብራሂም መሐመድን የንግድ እና የገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሾመዋል።

በተጨማሪም ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ የሴቶች ሕጻናት እና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል።

ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ 173 የሚሆኑ የወረዳ ዳኞች ሹመትን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በፍቅረሚካኤል ዘየደ እና ወንድሙ አዱኛ